የምንሰራው · What we do
- ቤት፣ አፓርትመንት፣ ቢሮ/ሱቅ፣ መሬት፣ መጋዘን፣ ገስት ሀውስና ነዳጅ ማደያ ለሽያጭና ለኪራይ · Property for sale and rent
- ገዢና ተከራይ ከሚፈልጉት ቤት ጋር ማገናኘት፤ የሚመስል ቤት ሲገባ ማሳወቅ · Matching buyers and tenants, with alerts
- ጽዳት፣ ቀለም፣ ፊኒሺንግ፣ ጂብሰም፣ ቧንቧ፣ ኤሌክትሪክ፣ ኔትወርክና ካሜራ · Home services
እንዴት እናረጋግጣለን · How we check listings
- ቤቱን በአካል እናያለን · We visit the property
- ካርታውን ወይም የውክልና ሰነዱን እንመለከታለን · We look at the title deed or power of attorney
- ከዚያ በኋላ ብቻ "በKINO በአካል የተረጋገጠ" እናደርገዋለን · Only then is it marked "verified by KINO"
የተለመዱ ጥያቄዎች · Questions
KINO ምንድነው? ምን ይሰራል?What is KINO and what does it do?
KINO Property & Services በአዲስ አበባ ቤት፣ አፓርትመንት፣ ቢሮ፣ ሱቅ፣ መሬት፣ መጋዘን፣ ገስት ሀውስ እና ነዳጅ ማደያ ለሽያጭና ለኪራይ የሚያገናኝ ድርጅት ነው። ጽዳት፣ ቀለም፣ ፊኒሺንግ፣ ጂብሰም፣ ቧንቧ፣ ኤሌክትሪክ፣ ኔትወርክና ካሜራ አገልግሎትም ያገናኛል።
KINO Property & Services connects buyers and tenants with homes, apartments, offices, shops, land, warehouses, guest houses and fuel stations for sale or rent in Addis Ababa. It also arranges cleaning, painting, finishing, gypsum, plumbing, electrical, network and CCTV work.
ማስታወቂያዎቹን እንዴት ታረጋግጣላችሁ?How do you check a listing?
ቡድናችን ቤቱን በአካል ሄዶ ያያል፤ የባለቤትነት ሰነዱን (ካርታ) ወይም የውክልና ሰነዱን ይመለከታል። "በKINO በአካል የተረጋገጠ" የሚል ምልክት የሚደረገው ይህ ከተደረገ በኋላ ብቻ ነው።
Our team visits the property and looks at the ownership document (title deed) or the power of attorney. A listing is marked "verified by KINO" only after this check.
ቤቴን እንዴት ላስተዋውቅ?How do I list my property?
በkino.et/sell ወይም በKINO ቴሌግራም ቦት ውስጥ ያለውን ቅጽ ይሙሉ፤ ፎቶዎችን ይላኩ። ገምግመን እንደውልልዎታለን፣ ቤቱን አይተን ካረጋገጥን በኋላ በዌብሳይቱ፣ በቴሌግራምና በሌሎች ገጾቻችን እናስተዋውቃለን።
Fill in the form at kino.et/sell or in the KINO Telegram bot and add photos. We review it, call you, check the property in person, and then promote it on the website, Telegram and our other pages.
የምፈልገውን ቤት እንዴት ላግኝ?How do I find the home I want?
በkino.et/want ወይም በቦቱ ውስጥ ሰፈር፣ መኝታ፣ በጀትና የክፍያ መንገድ ይንገሩን። የሚመስል ቤት ሲገባ በቴሌግራም እናሳውቅዎታለን።
Tell us the area, bedrooms, budget and payment method at kino.et/want or in the bot. When a matching home comes in, we tell you on Telegram.
ኮሚሽን መቼ ይከፈላል?When is commission paid?
ኮሚሽን የሚከፈለው KINO ባመጣው ገዢ ወይም ተከራይ ስምምነቱ ሲፈጸም ብቻ ነው። መጠኑ በምንፈራረመው የጽሁፍ ውል ላይ ይገለጻል።
Commission is paid only when a deal closes with a buyer or tenant that KINO introduced. The amount is written in the agreement we sign.
በምን አካባቢዎች ትሰራላችሁ?Which areas do you cover?
በመላው አዲስ አበባ፤ ለምሳሌ ቦሌ፣ ሲኤምሲ፣ አያት፣ ሰሚት፣ መገናኛ፣ ገርጂ፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ ሳርቤትና ካዛንቺስ።
All of Addis Ababa, for example Bole, CMC, Ayat, Summit, Megenagna, Gerji, Lebu, Jemo, Sarbet and Kazanchis.
ቤት ስገዛ ምን ልጠንቀቅ?What should I check before buying?
ዋናውን ካርታና የባለቤቱን መታወቂያ ሳያዩ ቀብድ አይክፈሉ፤ ካርታውን በሚመለከተው የመሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ያረጋግጡ፤ ስምምነቱን በጽሁፍ ይፈራረሙ፤ ክፍያውን በባንክ ይፈጽሙ። ለሕጋዊ ጉዳይ የሕግ ባለሙያ ያማክሩ።
Do not pay a deposit before seeing the original title deed and the owner's ID; confirm the deed at the land administration office; sign the agreement in writing; pay through a bank. For legal questions, ask a lawyer.
ጽዳትና ጥገና እንዴት አዝዛለሁ?How do I book cleaning or repairs?
በkino.et/service ወይም በቦቱ ውስጥ አገልግሎቱን፣ ቦታውንና ቀኑን ይምረጡ፤ ፎቶም ማያያዝ ይችላሉ። ዋጋና ቀን ለመነጋገር እንደውልልዎታለን።
Choose the service, place and day at kino.et/service or in the bot; you can add photos. We call you to agree the price and the day.
ያግኙን · Contact
📞 +251 994 51 53 53 · +251 911 48 15 68
✉️ info@kino.et
📍 አዲስ አበባ · Addis Ababa
